BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
የአሜሪካዋ ግዛት ምክር ቤት ለአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሰየመ
በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት 2' በግዛቱ የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን እንዲሆን የቀረበን የውሳኔ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ አፀደቀ። ይህ 'ኤችአር 441' የተሰኘው የውሳኔ ሐሳብ የፀደቀው ባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ነው።
ቀጥታ, ኢራን ጦርነቱን ለማስቆም የሚደረስ ስምምነት ሆርሙዝን ዳግም ለመክፈት ያስችላል አለች
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአሜሪካ ጋር ጦርነቱን ለማስቆም የሚደረገው ድርድር ላይ ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸውን እና ሆርሙዝምን ዳግም ለማስከፈት የሚያስችል መሆኑን ተናገሩ። ሰይድ አባስ አራጋቺ ለአገር ውስጥ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ስምምነቱ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ የተጣለው እገዳም እንዲነሳ ያደርጋል።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች
የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት እና በኋላ በተደረገ ምርመራ የተከለከለ ንጥረ ነገር እንደተገኘባት ካመነች በኋላ የአራት ወራት እገዳ ተጣለባት። የ29 ዓመቷ ጉዳፍ በ2022 የሴቶችን የ5,000 ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ስትሆን በ2023 ደግሞ የ10,000 ሜትር ውድድር አሸንፋለች።
በትግራይ ክልል የተረቀቀው ሕግ እና ስጋት የፈጠሩት በሞት የሚያስቀጡት አንቀጾች
በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሠራጨ ያለው እና ከስድስት ዓመት በፊት በተደረገው እና ለጦርነቱ እንደ አንድ ምክንያት በሚጠቀሰው ምርጫ የተቋቋመው የትግራይ ክልል አስተዳደር እንዳረቀቀው የሚነገርለት አዲሱ ረቂቅ አዋጅ አወዛጋቢ ሆኗል። "የትግራይ ሕዝብ ኅልውና እና ደኅንነትን ለማረጋገጥ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ያወጣው አዋጅ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ ሰነድ በክልሉ ምክር ቤት እንደሚጸድቅ ቢቢሲ ትግርኛ ከምንጮቹ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የዓለም ዋንጫ - 2026
አዳዲስ ታሪክ የሚመዘገብበት 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሙሉ መረጃን እዚህ ያገኛሉ
የዓለማችን ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር የዓለም ዋንጫ በ23ኛ ዙር ውድድር በርካታ አዳዲስ ነገሮች የሚታዩበት ሆኖ ከሰኔ 4 አስከ ሐምሌ 12 ድረስ ይካሄዳል። በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አገራት ውስጥ የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ ተጎራባቾቹ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያስተናግዱታል። የውድድር ቦታዎች፣ ቀናት፣ ሰዓታት፣ ውጤቶች፣ የምድብ ድልድል እና ደረጃ እንዲሁም ሌሎች የጨዋታ ዝርዝር መረሃ ግበሮች እዚህ ይቀርባሉ።
የሐኪም ማስረጃ የሚፈልጉ እና ፊፋ ወደ ዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች እንዳይገቡ የከለከላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች ወደ ሚካሄድባቸው ስታዲየሞች እንዳይገቡ በርካታ ነገሮች ላይ ክልከላ ጥሏል። እነዚህ የተከለከሉ ነገሮች ምንድን ናቸው? የተለየ ትዕዛዝ እና ፈቃድ የሚያስፈልጋቸውስ የትኞቹ ናቸው?
ፊፋ የክሪሚያን ካርታ ባለማካተቱ ይቅርታ ይጠይቀኝ ስትል ዩክሬን ከሰሰች
በቀጣናዊ ፖለቲካ ምክንያት እርስ በርስ የማይጫወቱ ሀገራት ስክሪን ላይ ሲታዩ ነው የክሪሚያ ሰርጥ የሌለበት የዩክሬን ካርታ የመጣው።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የሚፎካከሩት ዕጩዎች
በዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል ጎማ 2 ምርጫ ክልል ይወዳደራሉ። እርሳቸውን ለማሸነፍ የሌሎች ፓርቲ ዕጩዎችም ይፎካከራሉ። እነዚህ እጩዎች ከአሁን በፊትም ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የተወዳደሩ ናቸው?
ቪዲዮ, የኢትዮጵያ እና የሱዳን መካሰስ እና ፍጥጫ
ለረጅም ጊዜ ወዳጅ ሆነው የቆዩት ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነታቸው ሻክሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በይፋ በመውጣት ከመካሰስ አልፈው ወደ ግጭት የሚያመሩ ዛቻዎች እየተሰሙ ነው። ለመሆኑ ሁለቱ ጎረቤታሞችን እዚህ ያደረሳቸው ምንድን ነው?
ቪዲዮ, ከነዳጅ ጋር አብረው ስለሚነሱ ቁልፍ ነገሮች ምን ያህል ያውቃሉ?
ለዓለም የነዳጅ እና ኃይል አቅርቦት መሠረት የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የአገራትን ምጣኔ ሃብት ወዳልተጠበቀ ቀውስ እየወሰደው ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተደጋግሞ የሚነሳው ድፍድፍ ነዳጅ ምንድን ነው? የብሬንት ነዳጅስ? ዝርዝር መረጃው በዚህ ቪዲዮ እንመለከታለን።
ቪዲዮ, የደብረ ጽዮን በፕሬዝዳንትነት መሰየም ትግራይን ወዴት ይወስዳታል?
በትግራይ ሁለት ፕሬዝዳንቶች ተሹመዋል። ህወሓት የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት መፍረሱን በመጥቀስ ከጦርነት በፊት የነበረውን አስተዳደር መመለሱን አስታውቋል። ሌ/ጄኔራል ታደሰ በሥልጣን ላይ እያሉ ነው ደብረጽዮን ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት። ክልሉ እንዴት እዚህ ሁኔታ ላይ ደረሰ? የሌ/ጄነራል ታደሰ ዕጣ ፈንታስ ምን ሊሆን ይችላል?
ቪዲዮ, ቃላት እየተወራወሩ ያሉት ቱርክ እና እስራኤል ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ?
ባለፉት ሦስት ዓመታት ቱርክ እና እስራኤል መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመፍጠር ወደ ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭት እያመራ መሆኑ እየተነገረ ነው። በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል የቃላት ጦርነቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ ግጭት የመከሰት ዕድል ይኖራል ወይ የሚል ጥያቄን እያስነሳ ነው። የሁለቱ አገራት ውዝግብ ወዴት ያመራ ይሆን?
ቪዲዮ, ለሦስተኛ ጊዜ የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት
ቅዳሜ ምሽት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በርካታ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በተገኙበት የእራት ግብዣ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውሏል። ትራምፕን ለመግደል የሚደረግ ሙከራ አዲስ አይደለም። እስካሁን በፕሬዝዳንቱ ላይ የተቃጡት የመግደል ሙከራዎች ምን ይመስላሉ?
ቪዲዮ, የአሜሪካ እና የኢራን ተኩስ አቁም ስምምነት
ኢራን እና አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፍቶ መርከቦች እንዲያልፉ የሚያስችል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል። አገራቱን ሲያሸማግሉ የነበሩት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍ የተኩስ አቁሙ ወዲያውኑ ገቢራዊ እንደሆነ አስታውቀዋል። ሁለቱ አገራት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወሳኙን የባሕር መተላለፊያ ማክሰኞ ሌሊት ድረስ የማትከፍት ከሆነ “ሙሉ ሥልጣኔዋ ይወድማል” የሚል ዛቻ ካሰሙ ከሰዓታት በኋላ ነው። ለመሆኑ ስምምነቱ ለሁለቱ አገራት ምን ማለት ይሆን?
አነጋጋሪ ጉዳይ
በድምጻውያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ኤአይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ መልክ እንዴት ሊለውጠው ይችላል?
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ተገርበው በአዲስ መልክ የተሠሩ ሙዚቃዎች የዩቲዩብ ገፆችን ወርረዋል። የአንጋፋ እና ተወዳጅ ድምጻውያን የሙዚቃ ሥራዎች አማርኛው በተኮላተፈ የኤአይ አንደበት እየተዘፈኑ ነው። አንዳንዶቹ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዕይታዎች አሏቸው። የአድማጭን ትኩረት የሳቡም ይመስላሉ። ለመሆኑ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ልህቀት በተለይ በሙዚቃው ዘርፍ ምን ያሳጣ፣ ምን ያስገኝ ይሆን? የኢትዮጵያን ሙዚቃስ በምን መልኩ ሊለውጠው ይችላል?
በአርሲ የተፈጸመው ጥቃት ምርጫውን የማደናቀፍ አካል ነው - የጠ/ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
ንጹሐንን እና የሃይማኖት ተቋማትን ዒላማ በማድረግ የተፈጸሙ ጥቃቶች ዓላማቸው አገሪቱ እንዳትረጋጋ እና ምርጫውን ለማደናቀፍ የተደረገ ዕቅድ ተከታይ ነው ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽህፈት ቤት አመለከተ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርሲ ዞን ኦነግ ሸኔ በሰላማዊ ሰዎች እና በሃይማኖት ቦታዎች ላይ ፈጸማቸው ባሏቸው ጥቃቶች ለሞቱ እና ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ሰዎች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
"በአርሲ የሚስተዋለው በደልና ግፍ 'እስከ መቼ?' የሚል...ጥያቄን ፈጥሯል" - አቡነ ማትያስ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በምእመናን እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸመው ጥቃት መቀጠሉ "እስከ መቼ" የሚል ሐዘን እንደፈጠረ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት አስታወቁ። ባለፈው እሁድ እና ሰኞ በምሥራቅ አርሲ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች 13 የሚሆኑ ሰዎች ሲገደሉ፣ አንድ ቤተክርስቲያን በእሳት የወደመ መሆኑን እና ሌላ ቤተክርስቲያን ላይ ዘረፋ እና ጉዳት መድረሱን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በምሥራቅ አርሲ ሦስት ወረዳዎች በነዋሪዎች እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የደረሰው ምንድን ነው?
በምሥራቅ አርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተፈጸሙ ጥቃቶች 13 ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገረ ስብከት ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። የአካባቢው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ደያረጉ ሲሆን፣ የአካባቢው አስተዳደር ባለሥልጣናት ደግሞ ስለተፈጸመው ጥቃት እና ስለደረሰው ጉዳት መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ኢራን ከተነገረው በላይ በአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷን ቢቢሲ አረጋገጠ
ኢራን ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ ስምንት አገራት ውስጥ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከላትን ዒላማ አድርጋ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን፣ በአየር ላይ ነዳጅ የሚሞሉ አውሮፕላኖችን እና ራዳሮችን በመምታት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ውድመት አድርሳለች። ኢራን በአሜሪካ የጦር ተቋማት ላይ ያደረሰችው ጉዳት ከተነገረው በላይ መሆኑን የቢቢሲ ምርመራ አረጋግጧል።
ከፖለቲካዊ ፍጥጫ እስከ ወታደራዊ እርምጃ - በትግራይ ክልል ሊፈጠሩ የሚችሉ አራት ቢሆኖች
ህወሓት፤ ፌደራል መንግሥት ሕገ ወጥ ባለው ምርጫ የተቋቋመውን የትግራይ ክልል መንግሥት መመለሱን ተከትሎ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አደጋ ውስጥ የገባ ይመስላል። የክልሉ ሁኔታው አሁን ባለበት ይቀጥላል ወይስ ፌደራል መንግሥት እርምጃ ይወስዳል? ሥልጣን የተቆጣጠረው ህወሓትስ ወደ ወታደራዊ እርምጃ ይገባ ይሆን? ወይስ ሁለቱ አካላት አንዳች ስምምነት ላይ ይደርሳሉ?
መከላከያ ሠራዊት "ጽምዶ"ን በተመለከተ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ገለጻ መስጠቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት "ጽምዶ" በሚባለው እንቅስቃሴ በኩል "በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚቃጣ" ስጋት ቢኖር ስለሚወስደው እርምጃ አገር ውስጥ ለሚገኘው ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ማሳወቁን ገለጸ። የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር፤ ይህንን እንቅስቃሴ " 'ወደ መሬት እናወርዳለን' ብለው ስንዝር እንቅስቃሴ" የሚያደርጉ አካላትን አስጠንቅቀዋል።
ግብፅ "ከበባ እና ትንኮሳ በሚመስል መልኩ" እየተንቀሳቀሰች ነው ስትል ኢትዮጵያ ከሰሰች
ኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት አጀንዳዋን ይፋ ካደረገች በኋላ ግብፅ "ከበባ በሚመስል መልኩ" እየተንቀሳቀሰች ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ። አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ሐሙስ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን ካነሳች በኋላ ከግብፅ በኩል "ውጥረት፣ ትንኮሳ የሚመስሉ ነገሮች እየታዩ" መሆናቸውን ተናግረዋል።
'ቤተሰቦቼ ከሞትኩ በኋላ መርዶ ቢነገራቸው ይሻላል' - በሳዑዲ እስር ቤቶች የሞት ቅጣት የሚጠባበቁት ኢትዮጵያውያን
በሳዑዲ አረቢያ ሦስት ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ ክስ የሞት ፍርድ ሲፈጸምባቸው ቢያንስ 65 የሚሆኑት ደግሞ ፍርዳቸው ተፈጻሚ የሚሆንበትን ጊዜ እየተጠባበቁ መሆኑን ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የሳዑዲ መገናኛ ብዙኃን በካሃሚስ ሙሻይት ማረሚያ ቤት የሚገኙ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርድ እየጠበቁ መሆኑን ዘግበዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው እነዚህ ወጣቶች ከመርፈዱ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ይድረስልን ሲሉ ይማጸናሉ።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
አሜሪካ እና ኢራን ድል እንደተቀዳጁ እያወጁ ባሉበት ጦርነት አሸናፊው ማን ነው?
አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ማቆሟን እየተናገረች ነው። በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ከተደረገ ከሳምንታት በኋላ ማክሰኞ ዕለት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ "ኢፒክ ፊውሪ' በማለት የተጠራው ዘመቻ ማብቃቱን ተናግረዋል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በተደረገው ጦርነት ማን አሸነፈ?
መሪዎቹ እየተገደሉበት ባለበት ጸንቶ የቀጠለው የኢራን የጦርነት ወቅት አመራር የተዋቀረው እንዴት ነው?
ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል እየተፈጸመባት ባለው ጥቃት ከጠቅላይ መሪዋ ከአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጀምሮ በርካታ ቁልፍ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎቿ ተገድለውባታል። ነገር ግን አመራሯ ሳይፈረካከስ እየተተካካ ፍልሚያውን ቀጥሏል። ለመሆኑ የኢራን አመራር በዚህ ጦርነት ውስጥ ባለበት ጸንቶ እንዴት ሊቀጥል ቻለ?
ከየፈርጁ
'ወራጅ አለ'፡ የአሜሪካዊቷ ሙዚቀኛ የኢትዮጵያ ትዝታዎች
የኢትዮጵያን ሙዚቃ ማጣጣም ከጀመረች ከ20 ዓመታት በላይ አስቆጥራለች። አዲስ አበባ ደግሞ 11 ዓመታት ኖራለች። ኬታ ሆስታተር ትባላለች። ቫዮሊን ተጫዋች እንዲሁም ሙዚቃ አቀናባሪ ናት። ከሰሞኑ ‘ወራጅ አለ’ የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሟን ለቅቃለች። ስለ አዲሱ አልበሟ፣ ስለ አዲስ አበባ ቆይታዋ እና ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጋለች።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
አባቱን ገድሎ 12 ዓመት የተፈረደበት ልጅ ይቅርታ እንዲደረግለት የሚጠይቀው ቤተሰብ
የ27 ዓመቷ ሳራ ከእንባዋን ጋር እየታገለች ለግድያው ምክንያት የሆነውን አሳዛኝ ክስተት ለቢቢሲ ተናግራለች። ካርሎስ ለዓመታት ሞይሰስን እንደደበደበና አካላዊ ጥቃት እንደፈጸመበት የሰማችው ያኔ ነበር።
በአፍሪካ የፊልም አዋርድ ላይ የታየው ከ500 ዳቦዎች የተሰራው ቀሚስ
እሁድ ግንቦት 2 2018 ዓ.ም. በናይጄሪያ በተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ፊልሞች አዋርድ ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ የፊልም ባለሙያዎች እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ አልባሳት ተውበው ተገኝተዋል። በዕለቱ ከተገኙት ስመ ጥር ሰዎች ሁሉ ግን የአንዷ ታዋቂ የቴሌቪዥን ተዋናይ አልባሳት የበለጠ መነጋገሪያ ሆኖ አምሽቷል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች ማራቶንን ከሁለት ሰዓት ባነሰ ጊዜ እንዲጨርሱ ያስቻላቸው ምስጢር ምንድን ነው?
ትናንት እሁድ በለንደን የተካሄደው የማራቶን ውድድር ኬንያዊው ሳባስቲያን ሳዌ እና ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ሰዓት በታች ተከታትለው በመግባት ዓለምን አስደምመዋል።
አስፈላጊ ነገር ግን ጎጂ የሆነውን የጨው አወሳሰዳችንን እንዴት መመጠን እንችላለን?
ጨው ምግባችንን የበለጠ ያጣፍጠዋል። ለሰው ልጅ ሕይወትም አስፈላጊ ነው። በጨው ውስጥ የሚገኘው ሶዲየም በሰውነት ውስጥ የሚኖረውን ትክክለኛውን የውሃ መጠን ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ህዋሳትም ንጥረ ምግቦችን እንዲወስዱ ይረዳል። በምግብ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ፕሮግራም “ዘ ፉድ ቼይን” ጨው በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና እና ለአንድ ሰው ከመጠን በላይ የሚባለው የጨው ፍጆታ ምን ያህል ነው የሚለውን ተመልክቷል።
ከሆርሙዝ በፊት ዓለም ላይ ምን ያህል የባሕር እንቅስቃሴ እገዳዎች ተጥለዋል? ምን ያህል ውጤታማ ነበሩ?
አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡ እና የሚወጡ መርከቦች ላይ እገዳ መጣሏ ጥንታዊ የወታደራዊ ጫና መፍጠሪያ ስልትን መልሶ ያመጣ ነው። ይህ እርምጃ የባሕር መስመሮችን በመዝጋት ምጣኔ ኃብታዊ ጫና መፍጠር፣ ንግድን ማስተጓጎል እና ተገዳዳሪው አካል አቋሙን እንዲቀይር ወይም እጅ እንዲሰጥ የማስገደጃ ስልት ነው። ታሪክ የሚያሳየን እንዲህ ዓይነት ስልቶች ጫና በመፍጠር ረገድ ውጤታማ ቢሆኑም ሰፊ ተጽዕኗቸው ግን ከሚታሰበው በላይ ውስብስብ መሆኑን ነው።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!















































































































